Updated on: 14 January 2025
Description
መጽሐፍ ቅዱስ ሕያው እና ሥልጣን ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነው። በክርስትና ሕይወታችን ውስጥ በቃሉ እውነት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ እድገት ለማግኘት ከሁሉ የተሻለው መንገድ በጋራ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ውስጥ መካፈል ነው። ለዚህ እንዲመች መጽሐፍ ቅዱስን በጋራ የሚያጠኑ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቡድኖች አሉን። እነዚህ ትናንሽ፣ የበለጠ ቅርበት ያላቸው ቡድኖች የአዲስ ኪዳንን “ኅብረት” ማግኘት የምትችሉበትን እድል ይሰጣሉ። ማለትም በኢየሱስ ክርስቶስ የጋራ ሕይወታችንን መካፈል ነው። በዚህም መሰረት ለጊዘው ሁለት መርሀ ግብሮች አሉን፡፡ አንደኛው የአጋፔ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን ሲሆን ሁለተኛው የቤርያ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ነው፡፡
Schedule
የመጀመርያው ዘወትር ማከሰኞ ከ 18፡30 ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ሁለተኛው ዘወትር ሀሙስ ከ 18፡30 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
እርስዎም ምቹ የሆነውን ቡድን በመቀላቀል የእግዚአብሔርን ቃል ከኛ ጋር እንዲያጠኑ ተጋብዘዋል፡፡