Updated on: 02 January 2025
Description
የሚድያ ሚንስትሪ አገልግሎት በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በተለይ የቤተ ክርስትያንን ወንጌልን የማስፋፋት
ተልእኮዋን በመደገፍ እና በማጉላት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ አለው። በዚህ በዲጂታል ዘመን የሚድያ አግልግሎት የቤተክርስቲያንን መልእክት
ተደራሽነት ለማስፋት ጠቃሚ መሣሪያ ሆኖ ያገለግላል፣ ለዚህም ቤተ ክርስቲያናችን ልዩ ትኩረት ሰጥታ ትሰራለች፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ሰዎችን ለመድረስ፣ የአምልኮ ልምዶችን ለማጎልበት እና የቤተክርስቲያንን መልእክት ለውስጥ አባላትም ሆነ
ለሰፊው ህዝብ ለማስተላለፍ የተለያዩ ሚዲያ መድረኮችን - እንደ ማህበራዊ ሚዲያ፣ የቀጥታ ስርጭት፣ የኦዲዮ ቪዥዋል ፕሮዳክሽን እና
የታተሙ ቁሳቁሶችን ትጠቀማለች።
የሚድያ ሚኒስትርሪ ዓላማ የቤተ ክርስቲያናችን መልእክት ከደጃፋችን አልፎ ለብዙ ታዳሚዎች እንዲደርስ ማስቻል ነው።
ሚኒስትሪው በተለያዩ የሚዲያ መድረኮችን (ማህበራዊ ሚዲያ፣ ፖድካስቶች፣ የቀጥታ ስርጭቶች፣ ድረ-ገጾች፣ ወዘተ.)
በመጥቀም ወንጌልን ማሰራጨት ነው፡፡.
Schedule
For more information, you can reach out to us via WhatsApp!