Updated on: 13 January 2025
Description
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ቦን የእህቶች ህብረት አገልግሎት ካሉን ጠንካራ ህብረቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
የህብረቱ አላማ:-
ሴቶች እግዚአብሔር የሰጣቸውን ፀጋ እና ችሎታ በማወቅ እንዲጠቀሙና ለቤተ ክርስቲያን አልፎም ለምድር በረከት እንዲሆኑ መርዳት ነው፡፡
በተጨማሪም እኅቶች በሁሉም አቅጣጫ ዉጤታማ እንዲሆኑ ማገዝ ነው ::
Schedule
የእህቶች ህብረት የፕሮግራሞቹ ይዘት :-
የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት (እህቶችን መሰረት ያደረገ ጥናት )---> ሰኞ ከ ከ21: 00 - 22:00 በ online What'sApp group
ጸሎት---> ቅዳሜ ከ21:00 እስከ 22፡00 (በ online| What'sApp group)
በየወሩ መጨረሻ ቅዳሜ ከ 16:00 - 18:00 በአካል በመገናኘት የቤት ለቤት የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት እና እርስ በርስ የመተናነፅ ጊዜ
አመታዊ የእኅቶች ኮንፍራንስ
ልዩ ልዩ የአንድነት እና የፍቅር ጊዜ (ግሪል, የጋራ ጉዞ....)
በተጨማሪም የህይወት ተሞክሮዎቻቸውን ይከፋፈላሉ፤ ጌታ በህይወታቸው ያደረገውን ይመሰክራሉ። በዚህም እርስ በእርሳቸው ይተናነጻሉ።
የሴቶች ህብረት አገልግሎት በሁሉም እድሜ ያሉትን ሴቶች ያማከለ የጸሎት እና የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት የያዘ በመሆኑ ካሉበት ቦታ ሆነው ይቀላቀሉን፡፡